إعدادات العرض
ስነ-ምግባራዊ ፊቅህ
ስነ-ምግባራዊ ፊቅህ
1- አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።
2- አላህ ሁሉም ነገር ላይ መልካምነትን ጽፏል፤
3- ሰዎች ከቀደምት ነቢያት ካገኟቸው ቃላት መካከል ካላፈርክ የፈለግከውን ስራ! የሚለው አንዱ ነው።
4- በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውንም የጠላኸው ነገር ነው።
5- 'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?
6- አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።
8- ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።
9- ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን
10- አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል።
11- አትቆጣ!
12- ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው።
13- ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው መልካምን ተነፍጓል።
14- አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና።
15- ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።
16- ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።
17- ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።
19- በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!
20- ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።
21- ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።
24- በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና።
25- ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።
26- 'አላህ ጥንቁቅ፣ (ከሰዎች) የተብቃቃና ድብቅ የሆነን ባሪያ ይወዳል።'
27- 'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'
28- በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።
29- 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'
30- ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'
31- 'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!
33- ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።
34- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።
35- ዑመር ዘንድ ነበርንና እንዲህ አሉ: 'ከአቅም በላይ ከመጣጣር ተከልክለናል።'
38- አንድ ባሪያ የአንድን ባሪያ ነውር በዱንያ አይሸፍንም፤ የትንሳኤ ቀን አላህ ነውሩን የሚሸፍንለት ቢሆን እንጂ።
39- በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውን የጠላኸው ነገር ነው።" አሉኝ።
40- ሰዎች ከቀደምት ነቢያት ካገኟቸው ቃላት መካከል ካላፈርክ የፈለግከውን ስራ! የሚለው አንዱ ነው።
41- አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።
42- ሙስሊምን መስደብ አመፀኝነት ነው። መግደሉ ክህደት ነው።
43- የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።
44- በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና።
46- ውሸት መሆኑን እያወቀ ከኔ አንድ ሐዲሥን ያወራ ሰው ከውሸታሞች አንዱ ነው።
48- ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት!
49- ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።
50- ሆነ ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።
51- “የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።
52- ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።
62- ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል የባህሩን ውሃ የምታበላሽ የሆነችን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት።
63- አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ።
64- ተራጋሚዎች የትንሳኤ ቀን መስካሪዎችም ሆነ አማላጅ አይሆኑም።
65- ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው።
67- እኔ የተላኩት መልካም ስነምግባርን ላሟላ ነው።
