إعدادات العرض
የአምልኮ ፊቂህ
የአምልኮ ፊቂህ
2- እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ)
4- ግንኙነትና ፆታዊ ስሜትን የሚያነሳሱን ሳይፈፅምና ሳያምፅ ለአሏህ ሐጅ አድርጎ የተመለሰ ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን (ከወንጀል ንፁህ) ሆኖ ይመለሳል።
5- ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።
6- የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።
8- ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ ሪዛችሁን (የመንጋጭላ ፂማችሁን) ልቀቁ!
9- እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'
10- አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት
11- በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር
12- አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።
13- 'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'
14- ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።
15- (ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።
16- መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
17- ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።
18- የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው።
20- አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'
21- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሁሉም ሶላቶች በኋላ እነዚህን ውዳሴዎች ይሉ ነበር።'
22- 'ከነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራዎች ወደ አላህ ተወዳጅ የሚሆኑበት ምንም ቀን የለም።' ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ናቸው።
23- የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'
24- ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'
25- 'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'
26- እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡና
27- በሰባት አጥንቶቼ ሱጁድ እንዳደርግ ታዝዣለሁ።
29- አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም
30- 'ቁመህ ስገድ! ካልቻልክ ተቀምጠህ ስገድ! ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ። '
31- የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።
32- በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኋላ ነው።
34- እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና
36- ተረከዞቻቸውን የዉዱእ ውሃ የማያስነኩ ከእሳት ወዮላቸው! ዉዱእን አዳርሳችሁ አድርጉ!
37- 'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤
38- ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም።
39- 'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'
40- 'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'
42- የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።
43- (የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።
44- እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
45- ይህ የደም ስር መቆረጥ ነው። ባይሆን የወር አበባ ስታይበት በነበርሽው የቀናት ልክ ሶላትን ተይ! ከዚያም ታጠቢና ስገጂ።' አሏት።
46- ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።
47- አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
48- ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ።
49- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሊት የተነሱ ጊዜ አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁ ነበር።
50- መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ
51- አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!
53- የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና
54- የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄ በእጃቸው መካከል ሆኖ አንድን የቁርአን ምእራፍ እንደሚያስተምሩኝ ተሸሁድን አስተማሩኝ።
55- አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።'
56- 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪብ
57- ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።
59- የእውነት ሰማእትነትን እንዲሰጠው አላህን የጠየቀ ሰው ፍራሹ ላይ ቢሞት እንኳ አላህ የሰማእታትን ደረጃ ያደርሰዋል።
60- ከጀናባ አስተጣጠብ ሁኔታ
65- በአላህ መንገድ የሚዘምትን ያሰናዳ ሰው በርግጥም ዘምቷል። በአላህ መንገድ ለዘመተ ሰው (ቤተሰብ) በመልካም ትብብሩ የተተካ በርግጥም ዘምቷል።
66- የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው።
71- አላህ እንዲህ ብሏል: ‹ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለርሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለኔ ነው። በርሱ የምመነዳውም እኔው ነኝ።
75- አንዳችሁ የተኛ ጊዜ በማጅራቱ ላይ ሸይጧን ሶስት ቋጠሮ ይቋጥራል። በየሁሉም ቋጠሮ ላይም ረጅም ሌሊት አለና ተኛ! እያለ ይመታል።
76- ‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›
78- በአላህ መንገድ ሲታገሉ አቧራ የለበሱ እግሮችን እሳት ልትነካቸው አትችልም።
79- ሁለቱን የቀዝቃዛ ወቅቶች ሶላት የሰገደ ሰው ጀነት ገባ።
81- ጨረቃን ባያችሁ ጊዜ ፁሙ! ባያችሁት ጊዜ ፆም ፍቱ! ከተጋረደባችሁ ደሞ ልኩን ገምቱለት።
82- 'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች።
83- ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው ከኛ ገለል ይበል ወይም ከመስጂዳችን ገለል ይበል። ቤቱም ይቀመጥ" አሉ።
84- 'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?
85- ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!
87- የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።
88- የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው።
89- ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።
91- ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።
92- እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።
95- ፀሐይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም።
100- ከናንተ መካከል በርሱና በአላህ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጂ አንድም ሰው የለም
