إعدادات العرض
ቀልብን አርጣቢ ምክሮችና ተግሳጾች
ቀልብን አርጣቢ ምክሮችና ተግሳጾች
1- ስራዎች (ተቀባይነታቸው የሚለካው) በኒያ ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው የሚመነዳውም ባለመው ኒያ ልክ ብቻ ነው።
2- ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
5- አንዳችሁ ዝንባሌው ይዤ የመጣሁትን እስከሚከተል ድረስ አላመነም።
7- በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውንም የጠላኸው ነገር ነው።
8- 'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?
9- ትላልቅ ወንጀሎች፦ በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፣ ነፍስ ማጥፋትና የውሸት መሀላ ናቸው።
11- እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'
12- በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።
13- በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።
14- በሁለት መንገጭላዎቹ መካከል እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያሉትን አካላት (ሊጠብቅ) ዋስትና ለገባልኝ እኔም ጀነትን ዋስትና እገባለታለሁ።
15- ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።
16- ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።
17- ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው።
18- ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
19- አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።
20- ስራዎች የሚለኩት በኒያዎች (በሀሳብ) ብቻ ነው። ሁሉም ሰው የሚያገኘው ያሰበውን ነው።
21- በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።
23- ከኔ በኋላ ለወንዶች ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።
24- አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'
27- አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም
29- ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ!
31- የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው።
33- የእውነት ሰማእትነትን እንዲሰጠው አላህን የጠየቀ ሰው ፍራሹ ላይ ቢሞት እንኳ አላህ የሰማእታትን ደረጃ ያደርሰዋል።
34- አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።
35- የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም።
37- ይህ ከሰባ አመት ጀምሮ እሳት ውስጥ የተወረወረ ድንጋይ ነው። እርሱም እሳት ውስጥ ወደ ጥልቀቷ መጨረሻ ዛሬ እስኪደርስ ድረስ እየተምዘገዘገ ነበር።" አሉ።
39- የአላህ መልክተኛ ሆይ! መዳኛ ምንድን ነው? አልኳቸው። እርሳቸውም "ምላስህን ተቆጣጠር፤ ቤትህ ይስፋህ፤ በወንጀልህም ላይ አልቅስ!" አሉ።
40- 'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል።
41- አንዳችሁ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ሳያሳምር እንዳይሞት።
42- ከኔ በኋላ በናንተ ላይ ከምፈራላችሁ ነገሮች መካከል በናንተ ላይ የሚከፈትላችሁን የዱንያ ጌጥና ውበት ነው።
44- በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውን የጠላኸው ነገር ነው።" አሉኝ።
46- በዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገድ አላፊ ሁን።
47- ‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤
48- በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው።
51- የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል "አንዳች ነገር እንድጨምርላችሁ ትፈልጋላችሁን?
54- አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
55- ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል
56- የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።
57- ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት
59- እነዚያ ከቁርኣን የተመሳሰለውን የሚከተሉትን ከተመለከትሽ አላህ ተጠንቀቁዋቸው ብሎ የጠቀሳቸው እነሱ ናቸው።
60- ኃጢዓትን የሠራ ከዚያም ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ የሚሰግድ ከዚያም ለኃጢዓቱ ከአሏህ ምህረት የሚጠይቅ አንድም ሰው የለም፤ አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ።
61- {ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።}
74- ከዱንያ ቸልተኛ ሁን አላህ ይወድሃል። ሰዎች ዘንድ ካለው ቸልተኛ ሁን ሰዎች ይወዱሃል።" አሉት።
83- የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለድንገተኛ እይታ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም አይኔን እንዳዞር አዘዙኝ።
88- አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።
89- አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ።
91- አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት
92- እስልምና ላይ ሆኖ የሚበቃውን ያህል ሲሳይን የተለገሰና አላህ በሰጠውም የተብቃቃ ሰው በርግጥም ስኬታማ ሆኗል።
93- ከናንተ መካከል ሰውነቱን ጤነኛ ሆኖ፤ በነፍሱና በቤተሰቡ ላይ ደህና ሆኖ፤ የእለት ቀለቡ እርሱ ዘንድ ኑሮ ያነጋ ሰው ዱንያን በሙሉ እንደተረከባት ይቁጠር።
94- ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።
96- አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።
100- በአላህ ላይ አንዳችንም ላታጋሩ፤ ላትሰርቁ፤ ዝሙት ላትሰሩ፤
